የጦር ሜዳ

  • Read 3065 times
  • Print
  • Email

በእኔ አመለካከት ትርጉማቸዉ በፍጥነት እየተቀየሩ ከመጡ ሃሳቦች መካከል አንዱ “የጦር ሜዳ” የሚለዉ ነው። ቃሉ ለዘመናት ያገለገለዉ ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ወጣ ተብሎ ለጦርነት የሚያገለግልን ሥፍራ ለማመልከት ነዉ። የጥንት ጦርነቶች ከከተማ ቅጥሮች ዉጪ ተካሂደዉ፤ ያሸነፈዉ አካል ለምርኮና ለብዝበዛ ወደ ከተሞች ዘልቆ ይገባ ስለነበር ጦርነቶቹ የሚካሄዱበት የተለየዉ ሥፍራ ነዉ “የጦር ሜዳ” የሚባለዉ። አጠቃላይ ትርጉሙንና ልምዱ ለማሳየት እንጂ ከዚህ በተለየ መልኩ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ዘግናኝ ጦርነቶችም በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ነበሩ። በአጠቃላይ ግን “ጦር ሜዳ የሚሄድ ዘማች” እና “በቤት የሚቀር/በሰላማዊ ቦታ የዘወትር ተግባሩን የሚያከናዉን ዜጋ” የተለያዩ ነበሩ።

አሁን እንዲህ ያለ ነገር መቅረቱን በግልጽ እናስተዉላለን። ዓለም በሞላ የጦር ሜዳ ሆናለች። ያለንበት ማንኛዉም ቦታ (የሥራ፣ የገበያ፣ የመዝናኛ  ወ.ዘ.ተ.) በቅጽበት ወደ ጦር ሜዳነት ሊቀየር ይችላል። በጥቂት ቀናት ልዩነት የዋሽንግተን የባህር ኃይል መሥሪያ ቤትና የአሁኑ የጎረቤታችን ናይሮቢ ዘግናኝ እልቂቶች ይህንን ያመለክቱናል። ሰዎች በጠዋት ተነስተዉ ወደ ሥራ፣ገበያ፣ መዝናኛ እንጂ ወደ “ጦር ሜዳ” መሄዳቸዉን አላስተዋሉም። በነገራችን ላይ፣ ሰሞኑን እየታየ ባለዉ “ፊልም መሳይ” የሰላማዉያን እልቂት የተሰማኝ ሃዘንና የጸሎት ሸክም በቃል ልገልጸዉ አልችልም።

ታዲያ እንዲህ ባለ ዘመን፧-

አንደኛ ስለእያንዳንዷ ቀን የሕይወት ስጦታ፤ የሕይወታችንን ባለቤት እንድናመሰግን ሊያደርገን ይገባል። ሕይወትን እንደዘበትና እንደሚገባን ነገር አንቁጠር። በጦር ሜዳ ዓለም የተሰጠን ልዩ ጸጋ በመሆኑ ማመስገን ይገባል።

በሌላ በኩል ደግሞ የጌታችን ኢየሱስን ቃል ሊያስታዉሰን ይገባል (ማቴ 24፡6-7)። ጦርና የጦር ወሬ የመምጣቱ አንድ አመልካች/አስታዋሽ/ ደወል በመሆኑ ነቅቶ መኖርና መጠበቅ ይገባል።  “አትደንግጡ” ያለንን ጌታ ታምነን በእምነት “በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ፣ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” እንላለን። በተጨማሪም ለዘብተኛ መንፈሳዊነትን፣ ማፈግፈግን፣ መንፈሳዊ እንቅልፍን አስወግደን በትጋት ከጌታ ጋር እለት እለት መራመድ ግድ ነዉ። We can not afford to be weak or to backslide!

በመጨረሻም ክርስቶስን በግል በማመንና በመከተል መዳን ያስፈልገናል። ጌታን ስናምን ሞት አያስፈራንም፤ ምክንያቱም ከሁለተኛዉ ሞት (ከገሃነም) የተረፍን በመሆኑ። “ሞት ሆይ መዉጊያህ የት አለ” (2ቆሮ 15፡54) በሚል የትንሣኤ እምነት እንመላለሳለን።

በአጠቃላይ የዛሬዉ ምክሬ ይህ ነዉ፡- ዓለም ሁሉ ጦር ሜዳ ሆኗልና እንግዲህ ንቁ!

Last modified onThursday, 09 April 2015 20:31
Mamusha Fenta

Mamusha Fenta is a Bible expositor and conference speaker residing in Addis Ababa, Ethiopia.

Website: www.mamushafenta.com/

2 comments

  • Mimi
    Mimi Tuesday, 21 April 2015 09:00 Comment Link

    The right article on a right time

  • Mimi
    Mimi Tuesday, 21 April 2015 08:59 Comment Link

    The right article on a right time

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

Log in or Sign up