ምን እያልከኝ ይሆን?

  • Read 3122 times
  • Print
  • Email

መንገድ ላይ የቆመች መበለት ገፍቼ፣

“ምን ሆነሽ ነዉ?” ሳልል እንባዋን አይቼ፣

የጎዳናዉ ጩጬም “ስለእግዚአብሔር” ሲለኝ ፣

እርሱን ገላምጬ  ጊዜ ስለሌለኝ፣

መስኮቴን ዘግቼ ጩዀቱን አርግቤ፣

ወደቤትህ ልደርስ ላመልክህ ከልቤ።

ፍጥነቴን ጨምሬ ደጀሰላም ስደርስ፣

“ወድሃለሁ” የሚል የሕዝብህን ጩኸት

ተደምሬ ሳደርስ፣

ደስ እንድትሰኝም  ምስጋናዬን ሳጤስ፣

እጆቼን ዘርግቼ መስዋእቴን ሳፈሰዉ

ምን እያልከኝ ይሆን በሰማይ ያለኸዉ?

 

Last modified onThursday, 09 April 2015 20:48
Mamusha Fenta

Mamusha Fenta is a Bible expositor and conference speaker residing in Addis Ababa, Ethiopia.

Website: www.mamushafenta.com/

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

Log in or Sign up