የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ጠቅላላ ጉባኤ

  • Read 4230 times
  • Be the first to comment!

ጉባኤው የተካሔደው ከሚያዚያ 20-22 2007 ሲሆን ከመላው አገሪቱ አባል አብያተ ክርስቲያናትና ድርጅቶችን የወከሉ መሪዎች ተገኝተው ነበር። የጉባኤው መሪ ጥቅስ “ዘመናችንን እንደቀድሞ አድስ” (ሰቆ ኤር 5፡21) የሚል ሲሆን በሦስቱ ቀናት የጉባኤው የማለዳ ክፍለ ጊዜያት የጌታን ቃል በተከታታይ የማካፈሉ እድል ለወንድም ማሙሻ ተሰጥቶት ነበር።

በነዚሁ ቀናት “የቀድሞ ፍቅርን ስለ ማደስ” በሚል ርእስ ለጉባኤው መልእክት ቀርቧል። እግዚአብሔር የጠራን ‘ሙያተኛ አገልጋዮች’ እንድንሆን ሳይሆን አፍቃሪዎቹ እንድንሆን ነው። አገልግሎትና መሪነትም የፍቅር ምላሽ እንጂ የፍቅር ምትክ ሊሆኑ አይገባም። ጌታችን ለሎዶቂያ ቤ/ክ እንዳስጠነቀቀው ለብ ባለ ፍቅር ከኖርን የመተፋት እጣ ይጠብቀናል።

በመሆኑም ልባችንን መክፈትና ከእርሱ ጋር ሕብረትን በማድረግ ፍቅራችንን ማደስ ያስፈልገናል። እግዚአብሔር የሚያድስ አምላክ ነው። መመለስና ፊቱን መፈለግ ግን ይጠበቅብናል። የሚመጡት ዓመታት የቤተክርስቲያን የተሃድሶ ዓመታት ይሆኑ ዘንድ ከመሪዎች ብዙ ይጠበቃል። በጸሎትና በጾም ወደ ሕልውናው፣ ወደ ቃሉና ወደ መስቀሉ ሥራ መመለስ ያስፈልጋል የሚሉትና ሌሎች ተጨማሪ ትምህርቶች በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ቀርበዋል።

ተሳታፊ መሪዎችም በምልጃ ጸሎት ለመልእክቱ የሚገባውን ምላሽ ሰጥተዋል። 

እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይክበር!

Last modified onFriday, 22 May 2015 05:46

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

Log in or Sign up